Tuesday, August 28, 2012
ሕዝባዊ አሻራ ያረፈበት ታጋይ!!
ከታጋይ ሓዱሽ ካሡ ነሐሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም
ዓለማችን ክፋትና ደግነት፣ ሓዘንና ደስታ፣ ሰላምና ጦርነት፣ ልማትና ድህነት፣ የተደላደለና የጉስቁልና ኑሮ፣ ጨለማና ብርሃን ወዘተ የሚፈራረቁባት ናት፡፡ ቀንና ሌሊትም ስፍር ቁጥር የሌላቸው አስደሳችና አስከፊ፣ አንዳንዴም በፍፁም የማይገመቱና ለማመን የሚከብዱ ቅጽበታዊ ክስተቶች በየማይክሮ ሰከንዱ የሚስተናገዱባት ናት ዓለማችን፡፡
«የትያትር መድረኳ ዓለማችን» ዋነኛ ተዋናይ የሆነው የሰው ልጅ በየጊዜው የማህበራዊ ህግጋት የመለወጥ ብቃትና ችሎታ እንዳለው በተጨባጭ አሳይቷል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ዑደት፣ ሂደትና የተፈጥሮ ሕግጋት የሚጓዙት የመወለድ፣ የማደግና የመሞት ክስተቶችን፣ የመጨመርና የመቀነስ አልያም ወደ ºላና ወደፊት የመመለስ ሃይል ግን ለሰው ልጅ በፍጹም አልተቸረውም፡፡ ለዚህም ነበር! በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት የሚገኙት የኢትዮጵያ ህዝቦችና የተቀረው የዓለም ህዝብ ነሐሴ 14/2004 ዓ.ም ውድቅት ሌሊት አካባቢ ማለትም ከምሽቱ 5:40 ሰዓት ላይ ታላቁ ሕዝባዊ መሪ ታጋይ መለስ ዜናዊ ሲነጠቅ የሚሆነው ያጣው፡፡ ለዚህም ነበር! አርቆ አስተዋዩ፣ ብልሁና ታላቁ መሪ ታጋይ መለስ ዜናዊ ሲያሰቃያቸው ከነበረው ህመም አገግመው እንደ ትናንት ሁሉ በ2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይም በርቱዕ አንደበታቸው ለላቀ ውጤት ያዘጋጁናል ብሎ በተስፋ ሲጠብቅ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ፈጽሞ ያልገመተው እና ያልጠበቀው፣ አንጀቱን ያሳረረና ልቡን በሀዘን የሰበረ የሚወዳቸው መሪውን ቅጽበታዊ የመስዋዕትነት መርዶ ሳይወድ ተገዶ በድንገት እሬት እሬት እያለው የሰማው፡፡ በተከሰተው በዚሁ አስደንጋጭ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝቦች የተፈጥሮ ህግጋት ቀይ መስመር ማለፍ የእግር እሳት ቢሆንባቸውም፣ የታላቁ መሪያችን የታጋይ መለስ ዜናዊ ሀልፈተ ህይወት በይፋ ከሰሙበት ደቂቃ ጀምሮ በያሉበት ሆነው የብልሁ መሪያችን አስከሬን ወደ ሀገሩ ሲገባ በአካልና በመንፈስ በክብር ለመቀበል ግን አልተሳናቸውም፡፡
ለዚህም ነበር! በሃዘን ልባቸው የደማው የኢትዮጵያ ህዝቦች በያሉበት ሆነው እንባቸው ዱብ ዱብ እያለ ማለትም በየክልሉ የሚኖሩት ዓይናቸው በቴሌቪዥን መስኮት ተክለው የአስከሬኑን መግባት ሲጠባበቁ ያመሹት፡፡ ለዚህም ነበር! በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ደግሞ ያለማንም ጎትጓች የክረምቱ ዶፍ ዝናብ፣ ቁርና ብርድ ሳይበግራቸው ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት አደባባዮች ተሰልፎውና ሻማ አብርተው ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት የነበረውን የአስከሬን የክብር አቀባበል ስነ-ስርዓት እልህና ቁጭት በተሞላበት አኳኋን እንዲከናወን ያደረጉት፡፡ ህዝቡ የአርቆ አስተዋይ መሪው ህልፈተ ህይወት ከሰማበት ዕለት ጀምሮ በአስከሬኑ የአቀባበል ስነ-ስርዓት እንዲሁም አስከሬኑ በክብር ባረፈበት ቅጥር ጊቢ እና በያለበት ሆኖ ሐዘኑ በገለጸበት ወቅት አንደበቱን ከፍ አድርጎ የተለያዩ መዕልክቶች አስተላልፏል፡፡ ከብዙ በጥቂቱም የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ከጨለማ በማውጣት ብርሃን የፈነጠቀ የጀግኖች ጀግና ታጋይ መለስ ዜናዊ የጀመሩዋቸውን ስራዎች ከዳር እናደርሳለን!!
ባለራዕዩ ታጋይ መለስ ዜናዊ በአካል ቢለዩንም፣ ኢትዮጵያ ያለምንም ክፍተት ለቀጣይነት 40 እና 50 ዓመታት የሚያራምዱ የነጠሩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ቀርጾው ስለተወልን እንፅናናለን!! ህዝቡን ብቻ ተማምነህና ከጎንህ አሰልፈህ የደፈርኸው የህዳሴው ግድብ ሳትጨርሰው መቀጨትህ ቢቆጨንም
ቆሎ እየቆረጠምንም ቢሆን ከፍጻሜው እናደርሳለን!! እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!! መለስ ለሀገር -የለውም ወደር!! ታጋይ መለስ በመስዋእትነት ቢለየንም ትግሉ አይሞትም!! ጀግና አይሞትም!!
የኢትዮጵያ ህዳሴ ችቦው ታላቁ መሪያችን በአካል ቢለየንም ህያው ተግባሩና ራዕዩ ምንጊዜም አይሞትም!! የማይደፈረውን ዓባይ የደፈረ ጀግና! ታላቁ መሪያችን እንወድሃለን! አባይም ይገደባል!! ታጋይ መለስም
ዘላለም ይታወሳል!! ታጋይ ይወለዳል እንጂ አይኖርም!!
ጀግናው ታጋይ መለስ! አለት ላይ የተመሰረተ ህዝባዊ ታሪክ ለመስራት እንጂ ለመኖር አልታደለም!! በክፍለ ዘመን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ የተወደደና ህዝብ ልብ የገባ መሪ!! ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ዓለምም ያጣችው መሪ!!
ታላቁ መሪያችን ታጋይ መለስ የአፍሪካ አለኝታ!! የመላው ዓለም ግፉዓን ህዝቦች ዋልታና መከታ!! ታጋይ መለስ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ለፍትህ ታግለህ በመስዋእትነት ተለይተህ ጥለኸን በመሄድህ ብናዝንም አደራህን ተቀብለን ከጫፍ እናደርሳለን!!
የድሆች አባት፣ ሁሉንም ህዝቦች በእኩልነት የሚያይ፣ ለማህበራዊ ፍትህ የቆመ ቀናኢ እና አስተዋይ መሪ!! ታጋይ መለስ በ37 ዓመታት የውጣ ውረድ ጉዞ ለራሱ አንዲት ደቂቃ ሰጥቶ ሳያርፍ ለህዝቦች እፎይታ ሲል እንደ ሻማ የቀለጠ ውድ የህዝብ ልጅ ነው!!
አይቻልም እንጂ!! ዕድሜ ተቀንሶ የሚሰጥ ቢሆንማ ኖሮ - ለታላቁ መሪያችን ታጋይ መለስ ዜናዊ እንሰጠው ነበር!!
አይቻልም እንጂ!! አንዳንዶቻችን ሞተን ታጋይ መለስ ዜናዊ በህይወት ቢቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ይበልጥ ይጠቀም ነበር!!
ህዝቡ ከላይ የተገለፁትንና በርካታ መልዕክቶችን ድምጹን ከፍ አድርጎ በሚዲያ ማሰማቱ ብቻውን አላረካውም፡፡ ሳይውል ሳያድር በየቀየው የዕድር ድንኳን ጥሎ እንዲሁም በገዛ ፈቃዱ ከየቤቱ ግልብጥ ብሎ በየአደባባዩ ተሰብስቦ ግጥም፣ ቅኔ ቀረርቶና ፉከራ እያሰማ በእንባ እየተራጨ ሐዘኑን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ በ10 ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባ ነዋሪም በየቀኑ ማለትም ህፃናት፣ ሥራ የሌላቸውና ሥራ ያላቸው ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የስነ ጥበብ ሙያተኞች፣ ባለሃብት፣ ላብአደር፣ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አባላት፣ ምሁራን፣ ስፖርተኞች፣ ሲቪል ሠራተኛው፣ ሊስትሮው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም ዓቀፍ ድርጅት ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች በአጠቃላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በራሳቸው ፈቃድ እና ተነሳሽነት የታጋይ መለስ አስከሬን በክብር ያረፈበት ቅጥር ግቢ እንደ ሠራዊት እየተመሙ ሐዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
አንዳንዱ ሀዘን በርትቶበት በተለያዩ ምክንያቶች ተዝለፍልፎ በመውደቅ ጉዳት ቢደርስበትም ከወደቀበት እየተነሳ ጥልቅ ሀዘኑን ከመግለጽ የሚገታው ሃይል አልተገኘም፡፡ በንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራው ነጋዴና ባለሃብትም የሀዘን መግለጫ ወደ ሚዲያ ከመላክ ባሻገር የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን
ለመግለጽ ሲሉ በራሳቸው ፈቃድ ለተወሰኑ ቀናት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ገልጸዋል፡፡ በራሳቸው ፈቃድ ተቋሞቻቸውን ዘግተው አገልግሎት መስጠት ካቆሙት መካከል የምሽት መዝናኛ ክበባት የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡ በየክልሉ ያለው ህዝብ በበኩሉ በየአካባቢው ስርዓተ ቀብር ለማካሄድ መንግስትን እየጠየቀ ነው፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ ለመዝናናት ጊዜውም ፍላጎቱም የለውም፡፡ ሀዘን ላይ የወደቀው ህዝብ ዋነኛ አጀንዳ ታጋይ መለስ የቀረፀው ራዕይ በቁጭትና በእልህ እንዴት እናሳካው የሚል ብቻ ሆኗል፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ እንዲሁም ከላይ የተጠቆሙትንና ሌሎችም አባባሎች በመጠቀም በየአደባባዩና በያለበት ሆኖ ለታላቁ መሪያችን ለታጋይ መለስ ዜናዊ ያለውን ክብርና ጥልቅ ፍቅር መግለጽ የተለየ ትርጉም እንዳለው በገልህ ያሳየ ነው፡፡ ህዝቡ ተዓምር ባሰኘ አኳኋን ጥልቅ ፍቅሩን የገለጸው ታላቁ መሪ የገነቡዋቸው ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅትና መንግስት ያስመዘገባቸው የሚጨበጡና የሚዳሰሱ የሰላም፣ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ውጤቶች በተጨባጭ በማየቱ ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋም በየደረጃው የቱርፋቱ ተጠቃሚ በመሆኑ ነው፡፡ የቀጣይ ጉዞውም ብሩህ መሆኑ ወለል ብሎ ስለታየው ነው፡፡
በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት እንቅስቃሴዎች፣ አገላለጾችና አባባሎች አለጊዜያቸው ገና በ57 ዓመታቸው ለተቀጩት ለበሳሉና አርቆ አሳቢው ታጋይ መለስ ዜናዊ ዕድሜ ልካቸው ላከናወኗቸው በጎ ተግባራት የሚመጥኑ ተገቢ ምላሾች ናቸው ተብሎ በደፈናው ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ዋናው ቁምነገር ግን ምልዓተ ህዝቡ የታጋይ መለስ ግድብ መሆኑን ከማረጋገጡ ባሻገር እያንዳንዱ ዜጋ ለብልሁ መሪ ሀውልቱን በልቡ እንዳቆመለት የመሰከረበት ነው፡፡
ሆኖም ሀዝቡ ካስተላለፋቸው መልዕክቶች መካከል በአንድ መሠረታዊ አባባል ላይ ትንሽ ማለቱ አይከፋም፡፡ ይኸውም አይቻልም እንጂ!! ቢቻልማ ኖሮ!! ከእድሜአችን ተቀንሶ ወይም መተኪያ የሌለው ውድ ህይወታችን አሳልፈን ሰጥተን፣ የቁርጥ ቀን ልጃችን ታጋይ መለስ ለጥቂት ጊዜ እንኳን በቆየልን የሚለው አባባል ግን ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡
ይህም ከቀናት በፊት በመስዋእትነት የተለዩን አስተዋይ፣ ቆራጥና ብልህ መሪያችን የቀረጽዋቸውና ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብባቸው ያለ እረፍት ቀንና ሌሊት ደፋ ቀና ያሉላቸው ህዝባዊ የትግል መስመሮች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ባለቤታቸው የተወሰኑ የገዥው ፓርቲ አባላት ወይም የመንግስት አካላት ብቻ ሳይሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መሆናቸውን በተጨባጭ ያስመሰከረ ነው፡፡ በአጭር አገላለጽ ታጋይ መለስም በ80 ሚሊዮን ህዝብ እንደተተኩ በተግባር የታየበት ነው፡፡ ለምን ቢባል ከህጻን እስከ አዋቂ በታጋይ መለስ ዜናዊ መስዋእትነት ልቡ ቢደማም በህይወት እያሉ የጀመሩዋቸው ስራዎች እንጨርሳቸዋለን በማለት ተነሳሽነቱንና እልሁን በቁጭት በአንደበቱ ስለአረጋገጠ ነው፡፡ ይህ ህዝባዊ ተነሳሽነት በአንድ በኩል በዚህ ፈታኝ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከኢፌዴሪ መንግስት ጎን በአንድነት መቆማቸው፣ በሌላ በኩል ድርብ ድርብርብ ሃላፊነት እና አደራ የተሸከመው ባለተራው ተተኪው አመራርም ከሁሉም በላይ በቅድሚያ ህዝቡ ላሳየው አዎንታዊ ምላሽ ታላቅ ምስጋና ከማቅረብ ባሻገር፣ ቀደም ሲል የተጀመሩትን ብቻ ሳይሆን ያልተጀመሩ የህዳሴ ፕሮጀክቶች ካሉም በላቀ ሁኔታ መፈጸም እንዳለበት ያመለክታል፡፡
የታጋይ መለስ ግላዊና ፖለቲካዊ ሰብዕና፣ ማንነት እንዲሁም ተጨባጭ ተግባር በአራቱም ማዕዘናት ያሉት 80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሰጡት አጸፋዊ ምላሽ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአንደበቱ ከሰጠው ምስክርነት በላይ ለመግለጽ የሚያስችሉ ቃላት ቢፈለግ ማግኘቱ ከባድ ነው፡፡ ሆኖም ሩቅ አሳቢው ታጋይ መለስ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምረው እስከ ህልፈተ ሂወታቸው ድረስ አብሮአቸው ከዘለቀ ፖለቲካዊ መገለጫዎቻቸው መካከል ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው በአጭሩ ለመግለጽ ቢሞከር ድፍረት አይሆንም፡፡
ታጋይ መለስ ውስብስቡና በፍጥነት የሚለዋወጠው ዓለማዊ ሁኔታ በጥልቀት ተረድተው የሚተነትኑ፣ አጠቃላይ ሁኔታውም ከኢትዮጵያ ህዝቦች መሰረታዊ ችግሮች ያለውን ተያያዥነት በትክክል የሚቀምሩ፣ የሃገራችን ዋነኛ ጠላት የሆነው ድህነት ለይተው በማውጣት የትግል አገባቦች፣ የአጭርና የረዥም ጊዜ መፍትሄዎችን የማስቀመጥ ችሎታና ብቃት የተላበሱ ነበሩ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ታጋይ መለስ በትጥቅ ትግሉም ሆነ በሰላማዊ መድረኮች በቀረፁት የትግል መስመር ዙሪያ ሚሊዮኖችን በማሰባሰብና በሠራዊት መልክ በማደራጀት ከትግል ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን አፋኙን የደርግ ስርዓት ተዋግተውና አዋግተው የኢህአዴግን አላማ በአሸናፊነት እንዲወጣ ያደረጉ ናቸው፡፡ ለዘመናት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የኖረውን ድህነትም በቀረጹዋቸው ዘርፈ ብዙ ህዝባዊ ፖሊሲዎች እጁን እንዲሰጥ ያደረጉ መሪ ናቸው፡፡
ታጋይ መለስ ከአርቆ አስተዋይነታቸው በላይ በፖለቲካ ሰብእናቸውና ማንነታቸው ለየት የሚያደርጋቸው አንድ መሰረታዊና አብይ ጉዳይ ነበር፡፡ ይኸው በጣም ፈታኝና ወሳኝ በሚባሉት የትግል ምዕራፎች በተለይም ከእሳቸው እኩል ትግል የጀመሩ አንዳንዶች ጋራውን መውጣት እንዲሁም ቁልቁለቱን መውረድ አቅቷቸው እየተንሸራተቱ በአረንቋው ሲዘቅጡና በየንዑሳን ምዕራፎችም ሲንጠባጠቡ፣ ሲቸከሉ፣ አንዳንዶቹም ወደለየለት ፀረ-ህዝብ ጎራ ተቀላቅለው ህዝብን ሲያደሙ፣ ታጋይ መለስ ግን ባለፉት 37 የትግልና የድል ዓመታት ሰማይና ምድር የሚያናውጥ ከባድ ችግር ሲያጋጥም፣ ካነገቡት ህዝባዊ የትግል መስመር ለማይክሮ ሰከንድም ቢሆን ዝንፍ ሳይሉ በጣም ተስፋ አስቆራጭና ከባድ ፈተናዎችን ህዝባዊ ጽናት ተላብሳው እያለፉ የዘለቁ ታላቅ መሪ ናቸው፡፡ አንዱና ዋነኛው መለያቸውም ይህ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
ይህም እውነታ በዋነኛነት ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ /ህወሓት/ በ1977 ዓ.ም. በዋነኛነት ከጠራ የትግል መስመር እጦት የተነሳ በውስጣዊ ቸግሮች ተጠፍሮ የኋሊት ጉዞ ይዞ በነበረበት ጊዜ፣ ከውጭ ደግሞ ሶስት ጠላቶች ማለትም ደርግ፣ ድርቅና ሻዕቢያ ግንባር ፈጥረው በሚያዋክቡበት በዛ ቀውጢና ክፉ ወቅት፣ የህወሐት መሠረታዊ ችግር ምን እንደሆኑ ከችግር እንዴት መውጣት እንዳለበት በጥልቅ የተረዱት መለኛውና ብልሁ ታጋይ መለስ ዜናዊ የቀረጹዋቸው አዳዲስ ህዝባዊ የትግል መስመሮችና ወታደራዊ ዶክትሪኖች ድርጅቱንና ትግሉን ምን ጊዜም ከአደጋ እንዲወጣና የደርግ እድሜም እንዲያጥር ወሳኝ ድርሻ በመጫወት በህዝባዊ ገድሉ ሂደት ወሳኝና የማይረሳ አኩሪና ደማቅ ታሪክ በተግባራቸው እንዲጻፍ ያደረጉ መሪ ናቸው፡፡
ከዚህ ሌላ በ1993 ዓ.ም ህወሐት/ኢህአዴግን መበታተን አፋፍ ላይ አድርሰውት የነበሩት የስርዓቱ ዋነኛ አደጋዎች የሆኑት የኪራይ ሰብሳቢነት እና የፀረ-ዴሞክራሲ እነቅስቃሴዎችን በትክክል ተገንዝበውና በሳይንሳዊ መንገድ ተንትነው ኢህአዴግና አገርን ከብተና የታደጉ መሪ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ታጋይ መለስ የብሄር ልዩነቶች እርግማን ሳይሆኑ ፀጋ በመሆናቸው፣ እነዚህን አቻችሎ በዲሞክራሲያዊ አንድነት በሰላም መኖር እንደሚቻል በተግባር ያሳዩ መሪ ናቸው፡፡ ታጋይ መለስ ከቀደመ ነገሩ ለህዝቦች ጥቅም ያደሩ ስለነበሩ፣ በሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ የማይናወፅ አቋም ይዘው እያንዳንዱዋን ነገር የሚመለከቱዋትም ለኢትዮጵያ ህዝቦች ካላት ጥቅም እና ለሀገር ጥቅም ከሚኖራት ፋይዳ እና ትርጉም ነው፡፡
ባጭሩ ታጋይ መለስ ለህዝቦች ጥቅም ብቻ የወገኑ ፖለቲከኛና፣ ቆራጥ ህዝባዊና ጥበበኛ መሪ፣ በጉልበትና በሃይል ሳይሆን የጠራ አስተሳሰብ፣ እስክርቢቶና ወረቀት ብቻ ጨብጠው ጠንካራ የሃሳብ ትግል በማድረግ ሚሊዮኖችን በዙሪያቸው የሚያሰባስቡ፣ የትግል መስመር አፍላቂና የጦር መሃንዲስ፣ ኢኮኖሚስት፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪና ጠቢብ፣ ጋዜጠኛ፣ የተባ ብዕር ባለቤትና ስነፅሁፍ አዋቂ ወዘተ… በተሟላ መልኩ የተላበሰ ማንነትና ሰብዕና የነበራቸው ናቸው፡፡
«ስም ይቀድምዎ ለነገር» እንደሚባለው ታጋይ መለስ መጠሪያ ስማቸው በራሱ ተግባራቸውን በተሟላ አኳኋን ይገልጻል ቢባል ብዙም አከራካሪ አይሆንም፡፡
ይኸውም ታጋይ መለስ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ ከሚታወቁበት ስማቸውም በተጨማሪ ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸው ለገስ ዜናዊ የሚለውም ቢሆን ሰብዕናቸውና ማንነታቸው ይገልጻል፡፡ እንዴት ቢባል እንደሚከተለው በአጭሩ ሊገለጽ ይችላል፡፡
የሚወዱዋቸው የትግል ጓዶቻቸው ወደ ትግሉ በተቀላቀሉ ማግስት ያወጡላቸውና አስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ የዘለቀው መለስ የሚል መጠሪያቸው ትላንትም ሆነ ዛሬ ማንነታቸውና ተግባራቸው በትክክል የሚገልጽ ነው፡፡ እንዴት ቢባል በትጥቅ ትግሉ ወቅትም ሆነ በሰላማዊ የትግል መድረኮቹ ህወሐት/ኢህአዴግ መበታተን አፋፍ ላይ ሲደርስ በሳይንሳዊ ትንተና ከአደጋ አውጥተወ ወደ ተገቢው የትግል አቅጣጫ እንዲመለስ ሲያደርጉ የነበሩት በዋነኛነት ታጋይ መለስ መሆናቸው ማንም የሚመሰክረው ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በጥንታዊ ስልጣኔአቸው በዓለም ገናና ከነበሩት 10 አገሮች አንዷ የነበረች ኢትዮጵያ፣ በኋላቀር አስተሳሰብና ድህነት የተነሳ ላለፉት 1 ሺህ ያህልዓመታት ከሥልዕጣኔ ዕድገት ተገትታ ከተኛችበት አዘቅት ለማውጣት፣ በሳይንሳዊ አግባብ ገናና ታረኳን ለመመለስና ወደ ላቀ የስልጣኔ ማማ ለማድረስ «የኢትዮጵያን የህዳሴ መስመር በመቀየስ »ምልዓተ ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፈ በአንድ ልብ እንዲነሳሳ ያደረጉት ታጋይ መለስ በመሆናቸው መለስ የሚለው ስማቸው ሁለንተናዊ ተግባራቸውን ይገልጻል፡፡
ታጋይ መለስ ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸው የዳቦ ስማቸውም ቢሆን ትላንትም፣ ዛሬም ማንነታቸው ይገልጻል፡፡ ታጋይ መለስ ጨዋታና ነገር አዋቂ፣ ቀልደኛ፣ ሰው አክባሪ፣ ጎበዝ አንባቢ፣ ጥሩ አድማጭ፣ ትሁት ብቻ አልነበሩም፡፡ ከሁሉም በላይ ከውቅያኖስ የጠለቀ እና ከሰማይ አድማስ የሰፋ ዕውቀት ባለቤት ሆነው ሳለ፣ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ የማይወዱ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንደማንኛው ዜጋ የሚኖሩ፣ ከገበሬ ጋር ሲውሉ ገበሬ፣ ከወጣት ጋር ወጣት፣ ከምሁር ጋር ምሁር ወዘተ ሆነው የሚኖሩ፣ ዓይን አፋር፣ ለሰው አዛኝ፣ ሩህሩህና ለጋስም ነበሩ፡፡ እንዴት ቢባል አንድ ነገር ብቻ በማንሳት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይኸውም ከአመታት በፊት የሃገራችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የቀረጹት ፕሮግራም ውጤት በማስገኘቱ ተቀማጭነቱን ኖርዌ አገር ያደረገው “YARA Foundation” የተባለ ተቋም «የአረንጓዴ አብዮት አቀጣጣይ» በሚል ለግላቸው ያበረከተላቸውን 200 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሽልማት፣ ብሩህ አእምሮ እያላቸው በገንዘብ እጦት የተነሳ ዩኒቨርስቲ ገብተው መማር ያልቻሉት 550 ችግረኛ ሴት ኢትዮጵያውያን እንዲማሩበት ለግሰዋል፡፡ ይህንንና ተዘርዝሮ የማያልቅ ልግስናቸው ነበር ለገሰ የሚለው ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸው መጠሪያም ቢሆን ይገልጻቸዋል ቢባል አከራካሪ የማይሆነው፡፡
37 ዓመታት ሙሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ፈታኝ፣ እልህ አስጨራሽና ወሳኝ ህዝባዊና አገራዊ ችግሮች እንቅልፍ አጥተው ሲፈቱ እንዲሁም በግል የተሰጣቸው ሽልማት ሳይቀር ለችግረኞች መርጃ ሲለግሱ፣ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸውስ ምን አድርገው ይሆን? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው፡፡ መልሱ ግን አጭር ነው ከማቴሪያልና ገንዘብ አኳያ ምንም ነው፡፡ ይኸውም ሁሉም እንደሚያውቀው ለቤተሰቦቻቸው አባታዊ ፍቅር ከመስጠት ባሻገር በገንዘብ፣ በንብረትና በማቴሪያል የሚገለጽ ምንም ነገር አይገኝም፡፡ ከማቴሪያል አኳያ አለ ቢባል የታጋይ መለስ ዜናዊ ንብረት ወዳጅ ዘመድ የለገሱዋቸው መጻህፍት እና መደርደርያዎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጪ መኖሪያ ቤታቸው ቢፈተሽ የሚገኝ ቤሳ ቤስቲ የለም፡፡ በባንክም ቢሆን አንዲት ሳንቲም የላቸውም፡፡
በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትግል ወቅት ስለግል ሂወትና ንብረት ማሰብ ቦታ ስለአልነበረው ከላይ የተገለጸው ጉዳይ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም ሊባል ይችላል፡፡ ባለፉት 21 ዓመታት ግን ይሄ እውነታ እንዴት ሊሆን ቻለ? ታጋይ መለስ ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲመሩ ለምን ለግላቸው አላሰቡም? ቢባል መልሱ አሁንም አንድና አንድ ነው፡፡ ይኸውም ትግል ሜዳ ሲገቡ ለህዝቡ የገቡት ቃለመሃላና ሰማዕታት የሰጡዋቸውን አደራ እንደ ጠበል ጸዲቅ ተጠምቀውት ከራሳቸው የግል እና የቤተሰባቸው ሁኔታ ይልቅ ህዝባዊ ዓላማ ማሳካትን ከሁሉም በላይ ስለሚያረካቸው ለራሳቸው ጉዳይ ለአንዲት ሴኮንድም ብትሆን ማሰብ በማቆማቸው ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ለህዝብ ጥቅም ብቻ ያደሩ በመሆናቸው፣ በእንግሊዝኛው ቋንቋ “Self
less” የሚባለው ባህሪ ተላብሰው፣ ወዲህ ወዲያ ሳይሉ እና ለራሳቸው አንዲት ግራም የምትሆን ነገር እንኳን ሳያስቀሩ ራሳቸው እንደሻማ ቀልጠው ለማለፍ በራሳቸው ላይ ፈርደው ስለዘለቁ ነው፡፡
ለዚህም ነበር !አንዲት ግራም እስከምትቀረኝ ድረስ የኢህአዴግ ወታደር ነኝ! 6 ክንድ መሬት ስር ሳልገባ፣ በአበው አባባል ክንዴት ሳልንተራስ ኢህአዴግን አልለቅም እንዳሉ እስከወዲያኛው የዘለቁት፡፡ ታላቁና የህዝብ መከታው ታጋይ መለስ ዜናዊ የተመኙትንና ያሰቡትን በጥቂቱም ቢሆን በአይናቸው ለማየት በመብቃታቸው ያስደስተናል፡፡ ሆኖም በህይወት እያሉ የተመኙት እረፍት የማግኘት ጉዳይ እንደሰማይ እርቆአቸው ሳያገኙት ለዘላለማዊ እረፍት ብቻ መታደላቸው ግን ይቆጨናል፡፡ ሆኖም የታጋይ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ከሰሙበት ደቂቃ ጀምሮ፣ 80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝቦች እምባቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው በቁጭትና በእልህ ተነሳስተው እንደ የእድሜ እርከናቸው ልጃችን፣ ወንድማችን፣ አባታችን «ፈጣሪ መሬቱን ያቅልልህ» አናሳፍርህም!! «እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን» የሚል ድምጽ በአንድ ቃል በማሰማታቸው ሁላችንንም አፅናንቷል፡፡ በአንጻሩ ታጋይ መለስ ዜናዊ ከረዥም ዓመታት በፊት በተደጋጋሚ የኢህአዴግ መስመር የጥቂት ታጋዮች ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያ ህዝቦች ነው ሲሉት የነበረው ገሃድ ሆኗል፡፡ ታጋይ መለስም ህዝባዊ አሻራ ያረፈበት ታጋይ መሆናቸውን፣ ህዝቡ በህይወት እያሉም ሆነ በመስዋእትነት ከተለዩ በኋላም ቢሆን ደግሞ ደጋግሞ በአንደበቱና በተግባር አስመስክሯል፡፡ በመጨረሻም በልቤ አንድ ነገር ብቻ ተመኘሁኝ፡፡ ይኸውም ምን አለ በአሁኑ ሰዓት በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ያሉት የኢትዮጵያ ህዝቦች እንባቸው እንደ ጅረት ውሃ በጉንጫቸው በማፍሰስ ያሳዩዋቸውን ፍቅረ ንዋይና ያሳረፍባቸውን አሻራ ለአንድ ደቂቃ ያህል እንኳን ለዘለዓለሙ ካንቀላፋበት ቀና ብለው ቢመለከቱ ኑዛዜያቸው ምን ይሆን ነበር? ብዬ አሰብኩኝ፡፡ “እኔ ጉዞየን ጨርሼ በአካል ተለይቻችኋለሁኝ፡፡ ሆኖም በመንፈስ ለዘለዓለሙ ከእናንተው ጋር ነኝ፡፡ እኔን ጨምሮ ሁሉም ሰማዕታት የምትክሱት ግን በህዳሴ ችቦ ተለኩሰው የተጀመሩትን ዘርፈ ብዙ የሰላም፣ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለሴኮንድም ቢሆን ሳይቋረጡ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Ethiopian can not afford a prolonged war.
Ethiopian can not afford a prolonged war. Ethiopia as the poorest country in the world is dependent on aid. A prolonged war simply depletes ...
-
Ethiopia names 1st female deputy PM Source: Reporter Aster Mamo, executive committee member of the Oromo People's Democratic Organiza...
-
Addis Ababa, June 28 – Expansion project of Messebo Cement Factory that has been carried out at a cost of over 2.3 billion birr was i...
-
Wednesday, 29 August 2012 - African Development Bank approved a 251 million US dollar loan for Ethiopia. The two parties signed the loan agr...
No comments:
Post a Comment