አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 23፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምክር ያቋቋሟቸውን ኩባንያዎች ስራ አስፍተው እንደሚቀጥሉ የሜድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ገለፁ ።

የኩባንያው ሰራተኞች ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል ።
በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሀዝብ ማሰበን ፣ ህዝብን ማፍቀርንና ለህዝብ መስራትን ያስተማሩኝ መሪ ነበሩ ብለዋል ።
የኢትዮጵያ ህዝብ መሪውን ሲያጣ እኔ ደግሞ ቀኝ እጄን አጥቻለሁ ነው ያሉት ።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ እረፍት ያዘነው የኢትዮጵያ ህዝብም ውለታ የማይረሳ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል ።
በአቶ መለስ ምክር ያቋቋምናቸውን ኩባንያዎችንም ስራ በበለጠ አስፍተን አንቀጥላለን እናተም በርቱ ብለዋል የኩባንያውን ሰራተኞች ።
ተግተው በመስራትም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራእይ ለማሳካት በሰራተኛው ፊት ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ቃል መግባታቸውን የዘገበው ኤልያስ ተክለውልድ ነው ።
source: www.fanabc.com
No comments:
Post a Comment