5-23-23-የቦንድ ግዥና የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሰዒድ ያሲን የግል ኩባንያና ሠራተኞቹ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰዒድ ያሲን እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በበለጠ ተጠቃሚው የንግዱ ማኅበረሰብ ነው። ንግሥት ለግድቡ ግንባታ መላው ሕዝብ እንዲሳተፍ ላቀረበው ጥሪም ኩባንያው 100 ሺ ብር በስጦታ፣ 900ሺ ብር ደግሞ ከወለድ ነጻ የሆነ ቦንድ ለመግዛት ውሳኔ ላይ ደርሷል።የኩባንያው ሠራተኞች ደግሞ በአንድ ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ የአንድ ወር ደመዛቸውን 100ሺ ብር ለማበርከት ወስነዋል። በዓባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው የልማት ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት የነበረውን የረጅም ጊዜ ምኞት ያሳካ መሆኑን ጠቁመው፤ የኩባንያው ድጋፍ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
መላው የንግዱ ማኅበረሰብም በባለቤትነት መንፈስ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ሰዓድ ያሲን ኩባንያ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ንግድ ላይ የተሰማራ የአገር ውስጥ ኩባንያ ነው።
ነገሌ
በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞችና መምህራን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ980ሺ በላይ ብር ለመለገስ ቃል ገቡ፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ዋሬ ሰሞኑን እንደገለጹት፤ መምህራኑና ሠራተኞቹ ደመወዛቸውን ለመለገስ ቃል የገቡት በህዳሴው ግደብ ግንባታ ዙሪያ በስፋት ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡
እንዲሁም ከደመወዛቸው በተጨማሪ በግልና በቡድን እንደየአቅማቸው ገንዘብ በማዋጣት ቦንድ ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የህዳሴው ግድብ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም የሚፈለግባቸውን ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡
ዲላ
በጌዴኦ ዞን የቡሌ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞችና የአመራር አካላት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ብር ለገሱ።
ሠራተኞቹና የአመራር አባላቱ ደመወዛቸውን ለመለገስ የተስማሙት በግድቡ ግንባታ እንቅስቃሴ ዙሪያ በወረዳው ዋና ከተማ በስፋት ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡
እንዲሁም ሠራተኞቹ ከወር ደመወዛቸው በተጨማሪም ቦንድ እንደሚገዙና ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስም በገንዘባቸው፣ በዕውቀ ታቸውና በጉልበታቸው ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይሉ መንገሻ እንደተናገሩት፤ የመንግሥት ሠራተኛው ለህዳሴው ግድብ የሰጠው ድጋፍ ለሀገሩ እድገት ያለውን ጉጉት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ሠራተኛው የጀመረውን ተነሳሽነት በተሰማራበት መስክ ሁሉ በመተግበር ከድህነትና ኋላቀርነት ለመላቀቅ ለሚደረገው ድጋፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት አሳስበዋል።
source..http://www.ethpress.gov.et
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Ethiopian can not afford a prolonged war.
Ethiopian can not afford a prolonged war. Ethiopia as the poorest country in the world is dependent on aid. A prolonged war simply depletes ...
-
Ethiopia names 1st female deputy PM Source: Reporter Aster Mamo, executive committee member of the Oromo People's Democratic Organiza...
-
8/10/2012 The prolonged absence of Meles Zenawi, Ethiopia’s usually hyperactive prime minister, has sparked a covert succession struggle at ...
-
Addis Ababa, June 28 – Expansion project of Messebo Cement Factory that has been carried out at a cost of over 2.3 billion birr was i...
No comments:
Post a Comment