Friday, August 19, 2016

ህወሃት የብሄር ብሄረሰብ እኩልነትን የማይቀበሉ ሃይሎች የሚፈጽሙትን ህገወጥ ተግባር ከመላው ህዝብ ጋር እንደሚታገል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) ህገ መንግስታዊ ስርአትን በሁከት ለማፍራረስና የብሄር ብሄረሰብ እኩልነትን የማይቀበሉ የትምክትና የጠባብነት ሃይሎች የሚፈጽሙትን ህገወጥ ተግባር ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመቆም እንደሚታገል የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል።

አራተኛ አመት የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መታሰቢያን አስመልክቶ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ ህወሃት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ እነዚህ ሃይሎች የሚፈጽሙትን ማንኛውም ተግባር ከአጋር ድርጅቶቹና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦቹ ጋር በመሆን ህዝባዊ ፍርድ እንዲያገኙ አደርጋለሁ ነው ያለው።

ማእከላዊ ኮሚቴው በሰውና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳትም ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማው ገልጿል።

አራተኛ አመት የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሲከበር መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥና ልማትን ለማፋጠን የሚሰራውን ስራ በማጠናከር ነው ብሏል መግለጫው።

No comments:

Ethiopian can not afford a prolonged war.

Ethiopian can not afford a prolonged war. Ethiopia as the poorest country in the world is dependent on aid. A prolonged war simply depletes ...